ለኛስ

lanyaase-1

ለኛስ ማን ይዘን!?

አለ አደል በሀሳብ ሆናችሁ የምትሠሙት ድምፅ ፤ ሠምታችሁ ልብ የማትሉት ..... ልክ እንደዛ ይሠማኛል ..... "7ተኛው ጎዳና ፣ 7ተኛዉ ጎዳና ፣ ባንክ እየዘረፉ ነው!"..... ልብ ያላልኩት ድምፅ አሁንም ..... "7ተኛው ጎዳና ፣ 7ተኛዉ ጎዳና ፣ በእውነት ባንክ እየዘረፉ ነው!"........... ድጋሚ ማለቱ ይሆን - "በእዉነት" ማለቱ አሳምኖኝ ባላውቅም ዞሬ አየሁት ................. ወንድም አለም እርቃኑን ሆኖ ፥ ወገቡ በታጠቀው የገመድ ዝናር የጫት ገራባዎቹን በጎንዮሽ ወትፎ ፥ በቀኝ እጁ ሶምሶን 1000 ህዝብ የፈጀበትን መንጋጋ እንደ ስልክ ይዞ መረጃውን ያስተላልፋል ......... "በእውነት በእውነት ፥ ባንክ እየዘረፉ ነው!"......

ለምን ይሆን የሚደጋግምላቸው? አላመኑትም ይሆን? እንደውም መታመን ያለበት እሡ ነው! እብድ አደለ ....(common sense) የለበት ፤ ይሉኝታ የለበት እውነት እውነቷን ነው የሚያወራው ..... የሡ አለም....... ብቻውን ተጣልቶ ብቻውን ተስማምቶ ፣ እርቃንነት ሳያስፈራው በአደባባይ ዉሎ ፣ ድንበሬ ላይ ደረስክ ፥ ምን ታፈጣለክ ሳይባል ፣ ከፈለገ ግለሠብ ከፈለገ መንግስት ተሳድቦ (ለምን እንደሆነ ባይገባኝም መንግስትን የሚወድ እብድ አላጋጠመኝም) በነፃነት ይኖራል ....... አይ ያንተ አለም........ ግን እኛ እንዲ እንደምንታዘብህ አንተስ አልታዘብከንም? ሁላችንም 1 አይነት አልሆንብህም? የሆኑ ልብሳቸው የነፃ ውስጣቸው የቆሸሸ ሠዎች ፣ ጥላቻ የተሞሉ ግን አስመስለው የሚኖሩ ፣ ጩኸት ያላቸው ግን የታፈኑ ፣ መኖር መስራት መዞርን ፈልገው የማይችሉ የድንበር እሰረኞች .......... አይ እኛ እናዝናለን ደሞ ላንተ .... ለኛስ ማን ይዘንልን - ለመባላት ለቸኮልን .... ይቅርታን ለረሳን - እጃችንን ለሌላ ያነሣን

Comments (0)
No comments yet